ፋሲል ከነማ ከጅማ አባጅፋር – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ዘጠኝ ሰዓት የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎች ይዘንላችሁ ቀርበናል።

ቀጥተኛ የዋንጫ ተፎካካሪያቸው ኢትዮጵያ ቡናን አንድ ለምንም ረተው ለዚህኛው ጨዋታ የቀረቡት የፋሲል ከነማው አሠልጣኝ ስዩም ከበደ ለድሬዳዋው ውድድር ስንቅ የሚሆናቸውን ውጤት ለመያዝ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ እና ተጭነው ለመጫወት እንዳሰቡ በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው ተናግረዋል። ከቡናው ጨዋታም በአምስት ቢጫ ምክንያት ቅጣት ላይ የሚገኘውን ሀብታሙ ተከስተን በይሁን እንዳሻው ብቻ ለውጠው ለጨዋታው ቀርበዋል።

አሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም በበኩላቸው የፋሲልን ቡድን አድንቀው ለጨዋታው የተለየ ዝግጅት እንዳደረጉ እና ውጤታማ ለመሆን እንዳሰቡ ተናግረዋል። አሠልጣኙም ከመምራት ተነስተው ከተረቱበት የወልቂጤ ጨዋታ ሁለት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም አብርሀም ታምራት እና ሳዲቅ ሴቾን በሀብታሙ ንጉሤ እና ሙሉቀን ታሪኩ ተክተዋል።

ጨዋታውን ፌዴራል ዋና ዳኛ ኢሳይያስ ታደሰ በአልቢትርነት ይመሩታል።

የሁለቱ ቡድን አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሣሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
8 ይሁን እንዳሻው
10 ሱራፌል ዳኛቸው
17 በዛብህ መለዮ
7 በረከት ደስታ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም

ጅማ አባ ጅፋር

91 አቡበከር ኑሪ
28 ሥዩም ተስፋዬ
16 መላኩ ወልዴ
23 ውብሸት ዓለማየሁ
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
6 አማኑኤል ተሾመ
20 ሀብታሙ ንጉሴ
8 ሱራፌል ዐወል
10 ሙሉቀን ታሪኩ
19 ተመስገን ደረሰ


© ሶከር ኢትዮጵያ