ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና- አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የባህር ዳር ስታድየም የመጨረሻ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው አጠናክረናል።

ጉዳት ያጋጠመውን ሱራፌል ጌታቸውን በሄኖክ ገምቴሳ ብቻ ለውጠው ወደ ሜዳ የገቡት የድሬዳዋው አሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ በጊዮርጊሱ ጨዋታ የነበረባቸውን የአጨራረስ ችግር ለመቅረፍ ልምምዶችን እንደሰሩ በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው ተናግረዋል።

በባህር ዳር የነበራቸውን ቆይታ በውጤት ለማገባደድ እንዳለሙ የተናገሩት አሠልጣኝ ካሳዬ በበኩላቸው የፋሲልን ውጤት ሳያስቡ የራሳቸውን ሥራ ብቻ እየሰሩ ለመቀጠል ሀሳብ እንዳላቸው ተናግረዋለወ። ከፋሲሉ ጨዋታም ታፈሰ ሰለሞን እና አማኑኤል ዮሃንስን በፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን እና እያሱ ታምሩ ለውጠው ለዛሬው ጨዋታ ቀርበዋል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደቡት አርቢትር ናቸው።

የሁለቱ ቡድኖች የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
6 አወት ገብረሚካኤል
14 ያሬድ ዘውድነህ
21 ፍሬዘር ካሣ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
5 ዳንኤል ደምሴ
9 ሄኖክ ገምቴሳ
17 አስቻለው ግርማ
13 ኢታሙና ኬይሙኒ
99 ሙኅዲን ሙሳ
20 ጁንያስ ናንጄቦ

ኢትዮጵያ ቡና

99 አቤል ማሞ
11 አስራት ቱንጆ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
14 እያሱ ታምሩ
13 ዊሊያም ሰለሞን
15 ሬድዋን ናስር
3 ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን
17 አቤል ከበደ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን


© ሶከር ኢትዮጵያ