ሀዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎች አጠናክረን ቀርበናል።

በሰበታ ከተማ 2-1 ተረተው ለዚህኛው ጨዋታ የቀረቡት ሀዋሳዎች ከባለፈው ቋሚ አሰላለፍ ዘነበ ከድር እና ዩሃንስ ሰጌቦን በዳንኤል ደርቤ እና ወንድማገኝ ኃይሉ ተክተዋል። አሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትም በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው በባህር ዳር የነበራቸው የውጤት ቆይታ ጥሩ እንዳልነበረ ገልፀው ካሉበት ደረጃ ከፍ ለማለት አጥቅተው እንደሚጫወቱ ተናግረዋል።

ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ነጥብ ተጋርተው ለዚህኛው ፍሊሚያ የቀረቡት አሠልጣኝ ማሒር ዴቪድስ በበኩላቸው
በባህር ዳር በነበራቸው ቆይታ ጥሩ ቢንቀሳቀሱም አመርቂ ውጤት እንዳላገኙ አስረድተው ከዛሬው ጨዋታ ሦስት ነጥብ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። ነጥብ ከጣሉበት ጨዋታም ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም የአብስራ ተስፋዬ፣ ሮቢን ንግላንዴ እና አቤል እንዳለን አሳርፈው ከነዓን ማርክነህን፣ ሀይደር ሸረፋ እና ጋዲሳ መብራቴን ወደ ቋሚነት አሳርፈዋል።

ጨዋታውን የሚመሩት አልቢትር ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ብሩክ የማነብርሃን ናቸው።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ተከታዩን ይመስላለል:-

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
7 ዳንኤል ደርቤ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሃንስ
18 ዳዊት ታደሰ
23 አለልኝ አዘነ
29 ወንድማገኝ ማዕረግ
21 ኤፍሬም አሻሞ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ

ቅዱስ ጊዮርጊስ

22 ባህሩ ነጋሽ
14 ሄኖክ አዱኛ
15 አስቻለው ታመነ
6 ደስታ ደሙ
2 አብዱልከሪም መሐመድ
26 ናትናኤል ዘለቀ
5 ሀይደር ሸረፋ
21 ከነዓን ማርክነህ
11 ጋዲሳ መብራቴ
28 አማኑኤል ገብረሚካኤል
9 ጌታነህ ከበደ


© ሶከር ኢትዮጵያ