​የአሰልጣኞች አስተያየት | ድሬዳዋ ከተማ 1-3 ኢትዮጵያ ቡና

በባህር ዳር ከተማ አስተናጋጅነት ከተከናወነው የመጨረሻ የሊጉ ጨዋታ በኋላ አሰልጣኞች ለሱፐር ስፖርት ይህንን ብለዋል

አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ – ድሬዳዋ ከተማ

ስለጨዋታው

ከግማሽ መልስ ተጭነን ኳሶችን መንጠቅ መቻል ነበረብን። ነገር ግን ሁላችንም የአሰልጣኝ ቡድን አባላትም ተጫዋቾችም ጥሩ ስላልነበርን ጨዋታውን ልንሸነፍ ችለናል። ስለዚህ እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለሁ።

ስለ ቀጣዩ የዝግጅት ወቅት እና የመውረድ ስጋት

አሁን ያለንበት ቦታ በቂ ነው ብዬ አላስብም። እኛ ከሌሎቹ ቡድኖች በጣም መስራት እንዳለብን ያሳያል። ስለዚህ በቀጣዩ ጊዜ በሜዳችን እንደመጫወታችንም መጠን ተሻሽለን መጥተን ቡድኑ በሊጉ ላይ እንዲቆይ ለማድረግ ያለንን አቅም እንጠቀማለን።

አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ – ኢትዮጵያ ቡና

የሚፈልጉትን እንቅስቃሴ ስለመመለክተቻው

አዎ ጥሩ ነበር። እነሱ ከኋላ ወደ ፊት ኳስ እየቀየሩ ከኋላ ያሉትን ልጆች ለመቆጣጠር ነው የሞከሩት። ዋናው ማድረግ የነበረብን ነገር በዛ መሀል የሚቋረጡ ኳሶችን በመልሶ ማጥቃት ስለሚጠቀሙ ያንን መቆጣጠር ነበር። ሌላው ግን የእነሱ ፍፁም ቅጣት ምት አካባቢ ኳሱን ተቆጣጥረን መጫወት ችለናል። ያ ደግሞ ሂደቱን ሁሉ የሚጠቁም ነው። ሂደቱ ጥሩ ነበር ማለት ነው ፤ እዛ ጋር መቆጣጠር የምንችልበትን መንገድ መፍጠር ከቻልን። እና ጥሩ ነበር።

የአስራት እና እንዳለ ግብ ማስቆጠር

አዎ ጥሩ ነው። እኛ በምንጫወተው ጨዋታ ውስጥ የመጨረሻ ኳስ የሚጠይቁ ሰዎች እንዲበዙ እንፈልጋለን። ያ ለተጋጣሚ ከኋላ ለሚጫወቱ ተጫዋቾች አስቸጋሪ ነው ብለን ስለምናስብ። አንዱ ማረም የነበረብን እሱ ነው። ወደፊትም የመጨረሻ ኳስ የሚጠይቁ ሰዎች አቡኪ ብቻ ሳይሆን  ሌሎችም መጨመር አለባቸው። ያ ጥሩ አጋጣሚ ነበር።

ከሹመታቸው ጀምሮ በቡድኑ ላይ ለውጥ እያዩ ስለመሆኑ

አዎ ጥሩ ነው። እኛ ስንጫወት የመጫወቻ ቦታ እና ነፃ ሰው ለማግኘት የምንከፍታቸው ቦታዎች አሉ። እነዛን ክፍተቶች የማሻሻል እና ወደ ተጋጣሚ ግብ ስንሄድ የቁጥር ክምችት ሲገጥመን ያንን የማረም ጉዳይ ነው ፤ ሂደቱ ጥሩ ነው። በአብዛኛው በነበሩ ጨዋታዎች ውስጥ በምንፈልገው መንገድ ነው ማለት ባይቻልም በአመዛኙ ጨዋታውን እየተቆጣጠርን ነው። አንዱ ደግሞ ያ እንደዓላማ የያዝነው ነገር ስለሆነ ጥሩ ነው።

© ሶከር ኢትዮጵያ