አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

የሸገር ደርቢ የአሰላለፍ ለውጦች እና የተሰጡ አስተያየቶች ይህንን ይመስላሉ።

ኢትዮጵያ ቡናዎች ሰበታን ሲያሸንፉ ከተጠቀሙበት አሰላለፍ ውስጥ ሁለት ለውጦችን ሲያደርጉ ምንተስኖት ከበደ እና አማኑኤል ዮሀንስ በወንድሜነህ ደረጄ እና ሬድዋን ናስር ተለውጠዋል። አራፊ ከነበሩበት ሳምንት በፊት ከሰበታ ነጥብ ተጋርተው የነበሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ግን ምንም ለውጥ ሳያደርጉ ለጨዋታው ቀረበዋል።

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ፍራንክ ነታል የዕረፍቱ ጊዜ በአግባቡ ለማገገም እና ለመዘጋጀት ዕድል እንደሰጣቸው የተናገሩ ሲሆን ትልቅ ደርቢ እንደሆነ ቢያውቁም ሁሉም ጨዋታ ትልቅ መሆኑን እና በዛ ልክ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በተጫዋችነት እና አሰልጣኝነት የሚያውቁት ደርቢ ስሜቱ ከፍ ያለ እና ኃላፊነት ያለበት መሆኑን አንስተው በራሳቸው አጨዋወት ላይ እንዲሁም ስህተቶችን መቀነስ ላይ ያተኮረ ዝግጅት እንደነበራቸው ሲያነሱ የነጥብ ተቀራራቢነቱ ጨዋታውን ወሳኝ እንደሚያደርገውም ጠቁመዋል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።

የቡድኖቹ የዛሬው አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ኢትዮጵያ ቡና

99 አቤል ማሞ
11 አስራት ቱንጆ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
27 ያብቃል ፈረጃ
15 ሬድዋን ናስር
13 ዊሊያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
25 ሀብታሙ ታደሰ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን

ቅዱስ ጊዮርጊስ

22 ባህሩ ነጋሽ
6 ደስታ ደሙ
23 ምንተስኖት አዳነ
15 አስቻለው ታመነ
24 ፍሪምፖንግ ሜንሱ
20 ሙሉዓለም መስፍን
5 ሀይደር ሸረፋ
10 አቤል ያለው
21 ከነአን ማርክነህ
28 አማኑኤል ገ/ሚካኤል
9 ጌታነህ ከበደ


© ሶከር ኢትዮጵያ