አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ሀዋሳ ከተማ ከ ባህር ዳር ከተማ

የምሽት 1:00 ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እነሆ

አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምኅረት ወላይሃ ድቻን ከረታው ቡድናቸው የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በዚህ በሄኖክ ድልቢ፣ ዮሐንስ ሴጌቦ እና ቸርነት አወሽ ምትክ መስፍን ታፈሰ፣ ኤፍሬም አሻሞ እና ኤፍሬም ዘካርያስን በአሰላለፋቸው አካተዋል።

እንደባለፈው ሳምንት ጨዋታ ሁሉ ፋሲል ተካልኝን በዚህ ጨዋታም በኮቪድ ምክንያት የማያገኘው ባህር ዳር ከተማ በረዳት አሰልጣኙ ታደሰ ጥላሁን የሚመራ ሲሆን ካለፈው ሳምንት ጨዋታ ሁለት ለውጦችን በማድረግ በፍቅረሚካኤል ዓለሙ እና ሳለአምላክ ተገኘ ምትክ በረከት ጥጋቡ እና ወሰኑ ዓሊን የሚጠቀም ይሆናል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሤ ይመሩታል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍን እነሆ:-

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
7 ዳንኤል ደርቤ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሐንስ
23 አለልኝ አዘነ
3 ኤፍሬም ዘካርያስ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
17 ብሩክ በየነ
21 ኤፍሬም አሻሞ
10 መስፍን ታፈሰ

ባህር ዳር ከተማ

22 ፅዮን መርዕድ
3 ሚኪያስ ግርማ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
12 በረከት ጥጋቡ
8 ሳምሶን ጥላሁን
14 ፍፁም ዓለሙ
10 ወሰኑ ዓሊ
7 ግርማ ዲሳሳ
25 ምንይሉ ወንድሙ


© ሶከር ኢትዮጵያ