የአሰልጣኞች አስተያየት | ኮልፌ ቀራኒዮ 1-0 ሀምበርቾ ዱራሜ

የዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ ከተከናወነ በኋላ ከአሰልጣኞች ጋር ቀጣዩን ቆይታ አድርገናል።

አሰልጣኝ መሐመድኑር ንማ – ኮልፌ ቀራኒዮ

ስለጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ ነበር። እንደነበረን እንቅስቃሴ መጀመሪያ አጋማሽ ላይ መጨረስ ነበረብን። ብዙ ኳሶች ስተናል። በቀይም ወጥቶብን ነበር ፤ እንዳጠቃላይ ግን ጥሩ ነው። የምንፈልገውን ውጤት አግኝተናል ከፋጣሪ ጋር።

ስለዝግጅታቸው

ጥሩ ነው ማለት እንችላለን። በምንፈልገው ደረጃ አልተዘጋጀንም። ምክንያቱም የበጀት ችግር አለ ክለባችን ጋር። አንድ ሳምንት ነው የተዘጋጀነው። ስለዚህ በተወሰነ መልኩ ጥሩ ነበር ማለት እንችላለን።

አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ – ሀምበርቾ ዱራሜ

ስለጨዋታው

በጨዋታው እንደአጠቃላይ በተዘጋጀነው ልክ በሥነ-ልቦናው ረገድ ጥሩ አልነበርንም። የተቃራኒ ቡድን ደግሞ በዛው ልክ ጥሩ ነበሩ እንደጀመሩ። ያገኙትን አጋጣሚ መጠቀማቸው እኛን ጫና ውስጥ ከትቶናል። ያን ነገር ለማስተካከል ብዙ ጥረት አድርገናል። ብዙ የግብ አጋጣሚዎችንም ለመፍጠር ሞክረናል ነገር ግን ስኬታማ አልነበረንም። ተጫዋቾችም እንደጠበቅኳቸው አልነበሩም በጫና ነው የተጫወቱት። ምክንያቱን ባላውቅም ጫና ውስጥ ሆነው ነው የተጫወቱት። በቀጣይ የተሻለ ነገር ይዘን ለማምጣት እንሞክራለን። ዛሬ የነበረውን እንቅስቃሴ አሻሽለን እንቀርባለን። በሥነልቦናው ረገድ ጥሩ አይደለንም።