አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ወልቂጤ ከተማ ከ ሀምበሪቾ ዱራሜ

የሁለተኛ ሳምንት ሦስተኛ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እንዲህ ቀርበዋል።

በአሠልጣኝ ጻውሎስ ጌታቸው የሚመራው ወልቂጤ ከተማ ከጅማ አባጅፋር ጋር ነጥብ ከተጋራበት ቋሚ ስብስብ አንድ ተጫዋች ብቻ ለውጠዋል። በዚህም አህመድ ሁሴን ወጥቶ በሀይሉ ተሻገር ወደ ሜዳ ገብቷል። በሌላኛው የከፍተኛ ሊግ ክለብ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ ተረተው የሀዋሳ ቆይታቸውን የጀመሩት ሀምበሪቾዎች ሦስት ነጥብ ካስረከቡበት ጨዋታ ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ግርማ ታደሠ ርሆቦት ሶለሎ፣ በረከት ወንድሙ እና ብሩክ ኤልያስን አሳርፈው አምረላ ደልታታ፣ ሙሉነህ ገ/መድን እና አላዛር አድማሱን ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ አካተዋል።

ፌዴራል ዋና ዳኛ ዳንኤል ግርማይ ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል። የሁለቱ ቡድን አሠልጣኞች በቋሚነት ያሰለፏቸው ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተለው ነው።

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
12 ተስፋዬ ነጋሽ
19 ዳግም ንጉሴ
15 ዮናስ በርታ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
13 ፍሬው ሰለሞን
18 በሀይሉ ተሻገር
14 አብዱልከሪም ወርቁ
8 አቡበከር ሳኒ
7 አሜ መሐመድ

ሀምበሪቾ ዱራሜ

1 እሸቱ አጪሶ
15 እንዳለ ዮሐንስ
3 ሙሉነህ ገ/መድኅን
11 መስቀሉ ለቴቦ
25 አቤኔዘር ኦቴ
10 ነጋሽ ታደሰ
16 አላዛር አድማሱ
21 ፀጋአብ ዮሴፍ
8 ዋቁማ ዲንሳ
14 አምረላ ደልታታ
13 ዳግም በቀለ