ጅማ አባጅፋር አዲስ አሠልጣኝ ሾሟል

በፕሪምየር ሊጉ መክረሙን ያረጋገጠው ጅማ አባጅፋር ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አሠልጣኝ አግኝቷል።

ከአሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጋር የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን የጨረሰው ጅማ አባጅፋር አዲስ አሠልጣኝ ለመቅጠር ከሰሞኑን ሽር ጉድ ሲል ነበር። ክለቡ ከበርካታ አሠልጣኞች ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረ ቢሆንም ከደቂቃዎች በፊት አሸናፊ በቀለን ዋና አሠልጣኝ አድርጎ መሾሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ መከላከያ፣ ሲዳማ ቡና፣ አዳማ ከተማ (ሁለት ጊዜ)፣ ወላይታ ድቻ እና ሀዲያ ሆሳዕና አሠልጣኝ የነበሩት አሸናፊ በቀለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአሠልጣኝነት መንበርንም የወዘው እንደነበር ይታወሳል። አሁን ደግሞ መስቀል ፍላወር አካባቢ በሚገኘው ሙሴ ሆቴል ባደረጉት የመጨረሻ ድርድር ከስምምነት ደርሰው ክለቡን ለመያዝ ፊርማ አኑረዋል።