የጣና ሞገዶቹ የአጥቂ መስመር ተጫዋች አስፈርመዋል

እጅግ በንቃት በዝውውር ገበያው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች ስምንተኛ ተጫዋች አስፈርመዋል።

አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን ዋና አሠልጣኝ አድርገው የሾሙት ባህር ዳሮች በቀጣይ ዓመት ጠንክሮ ለመቅረብ ሐምሌ 1 የተከፈተውን የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት እየተጠቀሙ ይገኛሉ። ክለቡ ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ደግሞ ጋናዊው አጥቂ ኦሴ ማውሊን ውሀ ሰማያዊ ለባሾቹን ተቀላቅሏል።

በመቐለ 70 እንድርታ እና ፋሲል ከነማ የተጫወተው ማውሊ በዘንድሮው የውድድር ዘመን አጋማሽ ሰበታ ከተማን ተቀላቅሎ ግልጋሎት መስጠቱ አይዘነጋም። አሁን ደግሞ ለግማሽ ዓመት ያሰለጠኑትን አሠልጣኝ ተከትሎ ወደ ጣና ሞገዶቹ ቤት ጎራ ብሏል።