የጣና ሞገዶቹ ተከላካይ አስፈርመዋል

ባህር ዳር ከተማዎች ዘጠነኛ ፈራሚያቸው አድርገው ፈቱዲን ጀማልን የግላቸው አድርገዋል።

አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን አሠልጣኝ አድርገው የሾሙት ባህር ዳር ከተማዎች በዝውውር ገበያው ላይ በንቃት በመሳተፍ እስካሁም ስምንት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል። አሁን በተሰማ መረጃ ደግሞ የሲዳማ ቡናው የመሐል ተከላካይ ፈቱዲን ጀማል ባህር ዳርን ለማገልገል ፊርማ ማኖሩ ተረጋግጧል።

የቀድሞ የሀላባ ከተማ፣ ወላይታ ድቻ፣ ሲዳማ ቡና እና ኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች የነበረው ፈቱዲን በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ዳግም ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሎ ግልጋሎት መስጠቱ አይዘነጋም። ተጫዋቹ ከሲዳማ ጋር አንድ ዓሠት ቀሪ ውል የነበረው ቢሆንም በዛሬው ዕለት በስምምት በማፍረስ ውሃ ሰማያዊውን መለያ ለመልበስ ወደ ባህር ዳር ከተማ በሁለት ዓመት ውል አምርቷል። የፈቱዲን መፈረም ጥቂት የተከላካይ መስመር ስብስብ ለነበረው ባህር ዳር ጥሩ አማራጭ እንደሚሆን ይጠበቃል።