መከላከያ ወጣቱን የመስመር አጥቂ አስፈረመ

የመስመር አጥቂው አዲሱ አቱላ ወደ መከላከያ አምርቷል።

የአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ውል ካራዘመ በኃላ አራት አዳዲስ እና አምስት ነባር ተጫዋቾችን ለተጨማሪ ዓመት ያስፈረመው መከላከያ አምስተኛ ፈራሚ አድርጎ አዲሱ አቱላን ወደ ስብስቡ በዛሬው ዕለት አካቷል፡፡እግርኳስን በሲዳማ ቡና ከ17 ዓመት በታች በመጫወት በ2009 ጅማሮውን ያደረገው ወጣቱ አጥቂ በ2010 ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኃላ ያለፉትን አራት ዓመታት በዋናው የሲዳማ ቡና ቡድን ውስጥ በመጫወት አሳልፏል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት አዲሱ ተስፋዬ የሚለውን የስም መጠሪያውን የአባቱን በመለወጥ አዲሱ አቱላ ወደሚል ለውጦ የነበረው ወጣቱ ተጫዋች በአንድ ዓመት ውል ነው ጦሩን የተቀላቀለው፡፡