ሀዋሳ ከተማ የመስመር ተጫዋቹን ውል አድሷል

በአማካይ እና በመስመር ተከላካይ ቦታ መጫወት የሚችለው ተጫዋች በሀዋሳ ውሉን አራዝሟል፡፡

አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን ከቀጠረ በኋላ የስድስት ነባር ተጫዋቾችን ውል ያደሰው እና የስደስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር የፈፀመው ሀዋሳ ከተማ የዮሐንስ ሱጌቦን ውል ለሁለት ተጨማሪ ዓመት አድሷል፡፡ በ2008 ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ቡድን ካደገ በኋላ ያለፉትን ስድስት ዓመታት በክለቡ ዋናው ቡድን በመጫወት የቆየው የአማካይ እና የመስመር የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዘንድሮ በሀዋሳ ጥሩ አማራጭ በመስመር በኩል በመፍጠር አሰልፏል።

ዩሐንስ ውሉ ዘንድሮ መጠናቀቁን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር በባህርዳር ቆይታን አድርጎ ካጠናቀቀ በኋላ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት በሀዋሳ ለመቆየት ውሉን አራዝሟል፡፡