ኦኪኪ አፎላቢ ዝውውሩን ለመጨረስ አዲስ አበባ ገብቷል

ከሳምንታት በፊት ወደ ፋሲል ከነማ ለማምራት ስምምነት የፈፀመው ኦኪኪ አፎላቢ ዝውውሩን ለመጨረስ አዲስ አበባ ደርሷል።

2010 ላይ ከጅማ አባጅፋር ጋር የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ያነሳው ኦኪኪ አፎላቢ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት (ግማሽ) በሲዳማ ቡና ቤት ማሳለፉ ይታወቃል። ተጫዋቹ በአፍሪካ መድረክ ለመሳተፍ ካለው ፍላጎት የተነሳም የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊውን ክለብ ፋሲል ከነማን ለመቀላቀል ከሳምንታት በፊት ስምምነት ፈፅሞ ነበር። ይህ ስምምነት በፌዴሬሽን ፊት ህጋዊ እንዲሆንም ናይጄሪያዊው አጥቂ ዛሬ አዲስ አበባ መግባቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ድርድሮቹ ማለቃቸውን እና ሁለቱ አካላት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎም ተጫዋቹ በአሁኑ ሰዓት በሚገኝበት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ህጋዊ ውሉን ከደቂቃዎች በኋላ እንደሚፈፅም ይጠበቃል።