የሙሉዓለም መስፍን ታናሽ ወንድም አርባምንጭን ተቀላቅሏል

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ እንዳልካቸው መስፍን ወደ አርባምንጭ ከተማ አምርቷል፡፡

የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ውል ካራዘሙ በኃላ የበርካታ ነባር ተጫዋቾቹን ውል በማደስ እና አዳዲስ አምስት ተጫዋቾችን አስፈርሞ የነበረው አርባምንጭ ከተማ በዛሬው ዕለት ስድስተኛ አዲስ ተጫዋቹን በእጁ አስገብቷል፡፡ ከከፍተኛ ሊጉ በብዛት ወደ ክለቡ እየቀላቀለ የሚገኙት አዞዎቹ በቅርቡ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሲዳማ ቡና የተመለሰው ሙሉዓለም መስፍን ታናሸ ወንድም የሆነው አማካዩ እንዳልካቸው መስፍንን በሁለት ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡

ከጋሞ ጨንቻ የተስፋ ቡድን ከተገኘ በኃላ ያለፉትን ሦስት ዓመታት በአሰልጣኝ ማቲዮስ ለማ በሚመራው የጋሞ ጨንቻ ዋናው ቡድን በከፍተኛ ሊጉ ሲጫወት የምናውቀው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም ወንድሙ የተጫወተበትን ክለብ ተቀላቅሏል፡፡