መከላከያ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

ጦሩ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹን ስድስተኛ ፈራሚ በማድረግ ወደ ክለቡ ቀላቅሏል፡፡

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መሪነት በዝውውር ገበያው እየተካፈለ የሚገኘው መከላከያ ስድስተኛ ፈራሚ በማድረግ ደሳለኝ ደባሽን በአንድ አመት ውል አስፈርሟል፡፡ በአማካይነት በስሑል ሽረ እና ሰበታ ከተማ ከዚህ ቀደም መጫወት የቻለው ተጫዋቹ የተጠናቀቀው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግን ደግሞ ወደ ቀድሞ ክለቡ አዳማ ከተማ በመመለስ የአንድ ዓመት ቆይታን ማድረጉ አይዘነጋም። ከአዳማ ጋር ውሉን ያጠናቀቀው አማካዩ ከሁለት ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ማረፊያውን ጦሩ ቤት አድርጓል፡፡