አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጋና እና ከዚምባብዌ ጋር ለሚያደርጋቸው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጉን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ጥሪ ያደረጉላቸው ተጫዋቾች የፊታችን እሁድ (ነሐሴ 2) በካፍ የልህዕቀት ማዕከል ሪፖርት አድርገው አዳማ ላይ ዝግጅታቸውን እንደሚያደርጉም ተመላክቷል።

ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች ውስጥ ሰባቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ (እያንዳንዳቸው)፣ አምስቱ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሦስቱ ከባህር ዳር ከተማ፣ ሁለቱ ከወልቂጤ ከተማ እንዲሁም አንድ አንድ ተጫዋቾች ከጅማ አባጅፋር፣ ሲዳማ ቡና፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሀዋሳ የተካተቱ ናቸው።

ግብ ጠባቂዎች

ፋሲል ገ/ሚካኤል (ባህር ዳር ከተማ)፣ ፍሬው ጌታሁን (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ተክለማሪያም ሻንቆ (ሲዳማ ቡና) እና ጀማል ጣሰው (ወልቂጤ ከተማ)

ተከላካዮች

መናፍ ዐወል (ባህር ዳር ከተማ)፣ ያሬድ ባዬ( ፋሲል ከነማ)፣  አስቻለው ታመነ (ፋሲል ከነማ)፣ ደስታ ዮሐንስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ሱሌይማን ሀሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ረመዳን የሱፍ (ወልቂጤ ከተማ)፣ አሥራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና) እና ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

አማካዮች

ሀይደር ሸረፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ መስዑድ መሐመድ (ጅማ አባጅፋር)፣ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ታፈሰ ሰለሞን (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ዊሊያም ሰለሞን (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ይሁን እንደሻው (ፋሲል ከነማ)፣ ሀብታሙ ተከስተ (ፋሲል ከነማ)፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ) እና ፍፁም ዓለሙ (ባህር ዳር ከተማ)

አጥቂዎች

ሽመክት ጉግሳ (ፋሲል ከነማ)፣ አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ጌታነህ ከበደ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ) እና ሙጂብ ቃሲም (ፋሲል ከነማ)