በሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ለፍፃሜ የደረሱ ክለቦች ተለይተዋል

በሀዋሳ እየተደረገ ያለውን የኢትዮጵያ ሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የፊታችን ቅዳሜ በሚደረጉ የደረጃ እና የፍጻሜ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል፡፡

በሀዋሳ ከተማ ከሐምሌ 19 ጀምሮ በአስር ክለቦች መካከል በሁለት ምድቦች ተከፍሎ ሲደረግ የነበረው የኢትዮጵያ ሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና አስቀድሞ በተደረጉ ጨዋታዎች ስምንት ክለቦች ወደ 2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ማደጋቸውን ያረጋገጡ ሲሆን በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ግብርና ኮሌጅ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ለዋንጫ ፍፃሜ ያለፉ ሁለት ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል፡፡

ቀደም ብሎ 3፡00 ሲል በተደረገው ጨዋታ የአዲስ አበባ ከተማው አራዳ ክፍለ ከተማ ከምባታ ዞንን 1ለ0 ሲረታ የኦሮሚያ ክልሉ ሱሉልታ ከተማ ሀላባ ዞንን 4 ለ3 በማሸነፍ ወደ ፍፃሜው አልፈዋል፡፡

ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜ ነሀሴ 8 ረፋድ በሚደረጉ የደረጃ እና የፍፃሜ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል፡፡

ለደረጃ – ከንባታ ዞን ከ ሀላባ ዞን 3፡00
ለዋንጫ – አራዳ ክፍለከተማ ከ ሱሉልታ ከተማ 5፡00