ሲዳማ ቡና ሁለገቡ ተጫዋችን ለማስፈረም ተስማማ

የአማካይ እና የግራ መስመር ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ለሲዳማ ቡና ለመጫወት ተስማምቷል፡፡

የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌን ውል ካራዘመ በኃላ በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾች ያስፈረመውና የነባሮችን ውልም ያደሰው ሲዳማ ቡና የግራ መስመር ተከላካዩ እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሰለሞን ሀብቴን ለማስፈረም ተስማምተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በደደቢት፣ ወላይታ ድቻ እና ፋሲል ከነማ የተጫወተው ሰለሞን በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ደግሞ ለመቐለ 70 እንደርታ ለመጫወት ፊርማውን ያኖረ ቢሆንም በአካባቢው በተፈጠረ ችግር ምክንያት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ተካፋይ በነበረው መከላከያ ቆይታ በማድረግ ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲመለስ የክለቡ አካል የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ጦሩን ለቆ ወደ ሲዳማ ቡና ለማምራት ቅድመ ስምምነት ከክለቡ ጋር ተጫዋቹ ፈፅሟል፡፡ እስከ ነሐሴ 30 ድረስ በመከላከያ ውል ያለው ተጫዋቹ ውሉ እንደተጠናቀቀም የሲዳማ ቡና ተጫዋች መሆኑም የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡