መከላከያ የአማካዩን ውል አድሷል

አዲስ አዳጊው መከላከያ ከደቂቃዎች በፊት የአማካይ መስመር ተጫዋቹን ውል ማደሱ ተረጋግጧል።

በ2013 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ 38 ነጥቦችን በመያዝ ወደ ሀገሪቱ ከፍተኛ የሊግ እርከን ያደገው መከላከያ የነባር ተጫዋቾቹን ውል እያደሰ ጎን ለጎን አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ እየቀላቀለ እንደሆነ ይታወቃል። ቢሾፍቱ ላይ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የጀመረው ክለቡም ከደቂቃዎች በፊት የአማካይ መስመር ተጫዋቹ ግሩም ሀጎስን ውል ማደሱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አጋማሽ ላይ ከወሎ ኮምቦልቻ ጦሩን ተቀላቅሎ የነበረው ግሩም በአሠልጣኝ ዩሐንስ ሳህሌ ተፈልጎ ውሉን ለተጨማሪ አንድ ዓመት አድሷል።