ከቡናማዎቹ ጋር ነገ ወደ ዩጋንዳ የሚያቀኑ 20 ተጫዋቾች ተለይተው ታውቀዋል

በካፍ ኮፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ብናማዎቹ ቅድመ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ነገ ወደ ስፍራው ያቀናሉ።

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ከዩጋንዳው ዩአርኤ ጋር የተደለደሉት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ለስድስት ሳምንታት በቢሸፍቱ ከተማ ሲዘጋጁ ቆይተዋል። የፊታችን እሁድ ከሜዳቸው ውጭ የመጀመርያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ኢትዮጵያ ቡናዎች ነገ አመሻሽ ላይ ወደ ስፍራ ሲያቀኑ ከቡድኑ የሚጓዙት 20 ተጫዋቾች ተለይተው ታውቀዋል።

ግብጠባቂ

በረከት አማረ፣ አቤል ማሞ

ተከላካይ

ሥዩም ተስፋዬ፣ ወንድሜነት ደረጄ፣ አበበ ጥላሁን፣ ቴዎድሮስ በቀለ፣ አሥራት ቱንጆ፣ ኃይሌገብረ ትንሳኤ፣ ነስረዲን ኃይሉ

አማካይ

ታፈሰ ሰለሞን፣ አማኑኤል ዮሐንስ፣ ዊልያም ሰለሞን፣ ሬድዋን ናስር፣ ሮቤል ተክለሚካኤል፣ አቤል እንዳለ

አጥቂ

ያብቃል ፈረጃ፣ አላዛር ሽመልስ፣ እንዳለ ደባልቄ፣ አቡበከር ናስር፣ ሚኪያስ መኮንን

ከነገ ጉዞ ከሚያደርገው የልዑክ ቡድን አስቀድሞ አንዳንድ ጉዳዮችን አስቀድሞ ለመጨረስ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛህኝ ወልዴ አሁን ወደ ዩጋንዳ እያቀኑ መሆናቸውን አረጋግጠናል።