ድሬዳዋ ከተማ የግብ ዘብ አስፈርሟል

ድሬዳዋ ከተማዎች ልምድ ያለውን ግብጠባቂ አስፈርመዋል።

የመጀመርያ ምዕራፍ ቅድመ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተወሰኑ ቀናት ዕረፍት የሰጡት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት ግብጠባቂውን ደረጄ አለሙን ለአንድ ዓመት አስፈርመዋል።

ከግብጠባቂው ወንደሰን አሸናፊ ጋር በስምምነት ከተለያዩ በኋላ በቦታው ያለውን ክፍተት ለመሙላት ያሰቡት ድሬዎች ከቀናት በፊት ከቡድኑ ጋር በሀዋሳ ከተማ ሲዘጋጅ የቆየው ደረጄን አስፈርመዋል። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ፣ ዳሽን ቢራ፣ አዳማ ከተማ፣ ወልዲያ እና በሌሎች ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈው የግብ ዘቡ በያዝነው ዓመት ከደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር እስከተለያየበት ጊዜ ድረስ ሲጫወት ቆይቷል።

ከፍሬው ጌታሁን ጋር ብርቱ ፉክክር የሚጠብቀው ደረጄ ከዚህ ቀደም ከአሰልጣኝ ዘማርያም ጋር በወልድያ አብሮ መስራቱ ይታወሳል።