ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አዲስ አበባ ከተማ ጊዜያዊ አሰልጣኙን አስቀጥሏል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን የሚወዳደረው አዲስ አበባ ከተማ ጊዜያዊ አሰልጣኝ የነበረችው የሺሀረግ ለገሰን በዋና አሰልጣኝነት አስቀጥሏል።

የሺሀረግ ለገሰ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የዋና አሰልጣኟ ሙሉጎጃም እንዳለ ምክትል በመሆን ስታገለግል ከቆየች በኋላ የዋና አሰልጣኟ ስንብትን ተከትሎ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት የመጨረሻዎቹን የሊግ ሳምንታት መምራት ችላ ነበር።  አሁን ደግሞ ለቀጣዩ የ2014 የውድድር ዘመን በዋና አሰልጣኝነት እንድትመራ በቋሚነት ቀጥላለች። 

ክለቡ በተጨማሪም የክለቡ እና የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ቡድን ረዳት አሰልጣኝ የሆነው አሳምነው ገብረወልድ በረዳት አሰልጣኝነት በክለቡ እንዲቀጥል ወስኗል።