የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዋሳ ከተማ 1-0 ጅማ አባ ጅፋር

የዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታ በሀዋሳ 1-0 አሸነፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ ተጋጣሚ አሰልጣኞች ከሱፐር ስፖርት ጋር ቀጣዩን ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ – ሀዋሳ ከተማ

ከግቡ በኋላ ስለነበረው የቡድናቸው ሁኔታ

ጎሉን ካገባን በኋላ አጋጣሚዎችን አግኝተን ነበር። ያንን አለመጠቀማችን አንድ አስር አስራ አምስት ደቂቃ ወድ ኋላ እንድንሸሽ አድርጎናል። ዞሮ ዝሮ በሁለተኛው አጋማሽ አሻሽለን በምናገኘው ኳስ ለመሄድ ሞክረናል።

በቆሙ ኳሶች ለመጠቀም ስለመሞከራቸው

የቆሙ ኳሶችን የሚጠቀሙ ተጫዋቾች አሉን ፤ ሁለተኛ አማራጫችን ነው። እኛ ያሰብነው አንድ ሁለት ተቀባብለን በመልሶ ማጥቃት ለመሄድ ነው። ጎል ያገኘነውም በዛ አጋጣሚ ነው።

ስለቡድናቸው እንቅስቃሴ ከተጋጣሚ አንፃር

ጅማ ታክቲካሊ ዲሲፕሊንድ ነው። የመጫወቻ ቦታ እየከለከለን ነበር። ያንን በቅብብል ለማለፍ ነበር። እውነት ለመናገር ሜዳውም ተፅዕኖ ነበረው ፤ ሳሩ አድጓል። ያ በመሆኑ እና ተቀራርበው ስለሚጫወቱ ጀርባቸውን ለመጠቀም ነበር ያሰብነው። ዞሮ ዞሮ ያው ሦስት ነጥብ ነው ፤ ተሳክቷል።

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ – ጅማ አባ ጅፋር

ስለቡድናቸው የመጨረስ ብቃት

የሳትናቸው ኳሶች ያስቆጫሉ። ግን ደግሜ ፊት ላይ ያሉት ተጫውቼች እንደወጣትነታቸው ከእነሱ ተስፋ ሰጪ ነገር አያለሁ። ለሀገር ብዙ ይጠቅማሉ ብዬ አስባለሁ። በቀጣይ ደግሞ ለማስተካከል እንሞክራለን።