አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | አዲስ አበባ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ሦስተኛ ጨዋታን አሁናዊ መረጃዎች እንድትካፈሉ ጋብዘናል።

በሦስተኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብር አብረው ወደ ሊጉ ያደጉትን መከላከያ ሦስት ለምንም ያሸነፈው አዲስ አበባ ከተማ ከድል ጋር ከታረቀበት ጨዋታ ሦስት ለውጦችን አድርጎ ዛሬ ወደ ሜዳ ይገባል። በዚህም አምበሉ ኢያሱ ለገሠን ጨምሮ ሳዲቅ ተማም እና ብዙአየሁ ሰይፉ አርፈው ሳሙኤል አስፈሪ፣ ኤሊያስ አህመድ እና እንዳለ ከበደ ጨዋታውን ለመጀመር ተዘጋጅተዋል።

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊዎች ፋሲል ከነማዎች በበኩላቸው ጅማ አባጅፋር ላይ አራት ግቦችን አስቆጥረው ካሸነፉበት ጨዋታ ተከላካዮቹ አብዱልከሪም መሐመድ እና አስቻለው ታመነን እንዲሁም የመስመር ተጫዋቹ ሽመክት ጉግሳን በሰዒድ ሀሰን፣ ይሁን እንዳሻው እና ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ተክተው ወደ ሜዳ ገብተዋል።

የአዲስ አበባው አሰልጣኝ ደምሰው ፍቃዱ ዕረፍቱን በተቻለ መጠን ለመጠቀም መሞከራቸውን እና በዋና አሰልጣኝነት የተሰጣቸውን ኃላፊነት እየተወጡ እነደሆነ ገልፀው ፋሲል የሊጉ መሪ ቢሆንም ከመከላከያ ጋር ያሳዩትን አቋም ጠብቀው ለመቅረብ እንደሚሞክሩ ተናግረዋል። አሰልጣኝ ሥዩም በበኩላቸው ዕረፍቱ የታመሙ እና ብዙ የተጫወቱ ተጫዋቾች እንዲያገግሙ ማድረጉን በበጎው እንደሚያዩት ገልፀው ከጨዋታ ቢርቁም በማሸመፍ ሪትም ውስጥ እንደሚቀጥሉ እርግጠኛ መሆናቸውን አንስተዋል። ከየመን መልስ አዲስ አበባን ወደ ሊጉ መመለሳቸውን አስታውሰው ዳግም በሊጉ መታየቱ ደስ ቢያሰኛቸውም ለማሸነፍ እንደሚገቡ ተናግረዋል።

ፌዴራል ዳኛ ተከተል ተሾመ በአልቢትርነት በሚመሩት ጨዋታ ላይ ከድል መልስ እርስ በእርስ የተገናኙት ሁለቱ ቡድኖች የሚጠቀሟቸው የመጀመሪያ ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተለው ነው።

አዲስ አበባ ከተማ

30 ዳንኤል ተሾመ
14 ልመንህ ታደሰ
6 አሰጋኸኝ ጽጥሮስ
2 ሳሙኤል አስፈሪ
18 ሙለቀን አዲሱ
20 ቻርለስ ሪባኖ
16 ያሬድ ሀሰን
9 ኤሊያስ አህመድ
7 እንዳለ ከበደ
10 ፍፁም ጥላሁን
29 ሪችሞንድ አዶንጎ

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
13 ሰዒድ ሀሰን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባዬ
21 አምሳሉ ጥላሁን
8 ይሁን እንደሻው
14 ሀብታሙ ተከስተ
17 በዛብህ መለዮ
7 በረከት ደስታ
18 ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ
9 ፍቃዱ ዓለሙ