ከፍተኛ ሊግ | የካ ክፍለ ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ላይ የተደለደለው የካ ክፍለ ከተማ አስራ አንድ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአስራ አራት ነባሮችን ውል አድሷል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከሚገኙ ክለቦች መካከል የመዲናይቱ ክለብ የካ ክፍለ ከተማ አንዱ ነው፡፡ በሊጉ ምድብ ሐ ስር ተደልድሎ ያለው ክለቡ ለ2014 የውድድር ዘመን ተጠናክሮ ለመቅረብ በማሰብ የአሰልጣኝ ባንተይርጋ ጌታቸውን ውል ያራዘመ ሲሆን ተጨማሪ ረዳት አሰልጣኝም ወደ ቡድኑ አካቷል። ወደ አስራ አንድ አዳዲስ ተጫዋቾችንም ከተለያዩ ክለቦች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

ታደሰ ያለው (ግብ ጠባቂ ከቆቦ ከተማ) ፣ ኩን ሮች (ግብ ጠባቂ ከአራዳ ክ/ከተማ) ፣ ኤፍሬም ጌታቸው /ተከላካይ ጅማ አባ ቡና) ፣ ዘላለም በረከት (ተከላካይ ከጎጃም ደ/ማርቆስ) ፣ በረከት ታምራት (አማካይ ከሮቤ ከተማ) ፣ ካሳሁን ገ/ሚካኤል (አማካይ ከደቡብ ፖሊስ) ፣ ቢንያም ካሳሁን (አማካይ ሀዋሳ ከተማ U 20ዘ ፣ አማኑኤል ግዛቸው (አጥቂ ከደሴ ከተማ) ፣ ሀምዛ አብዱራህማን (አጥቂ ጅማ ጊቤ) ፣ መስፍን ዳንኤል (አማካይ) እና ብስራት በቀለ (አጥቂ ከአረካ ከተማ) የክለቡ አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ናቸው፡፡

ቡድኑ ከአዲስ ፈራሚዎች በተጨማሪ የአስራ አራት ነባር ተጫዋቾችን ውል እንዳደሱም ሶከር ኢትዮጵያ ክለቡ ከላከላት መረጃ ተገንዝባለች፡፡