\”የዛሬውን ጨዋታ በተሻለ ትኩረት ለመጫወት በሚረዳን ልክ ተዘጋጅተናል ብዬ አስባለው\” ከነዓን ማርክነህ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የመጨረሻ ጎል ያስቆጠረው ከነዓን ማርክነህ ከጨዋታው በፊት የመጨረሻ ሀሳቡን የሰጠን ተጫዋች ነው።

ለዛሬው ጨዋታ ስለተደረገው ዝግጅት…

እንዳያችሁት ለጊኒው ጨዋታ በጥሩ ሁኔታ እየተዘጋጀን እንገኛለን። የዛሬውንም ጨዋታ በተሻለ ትኩረት ለመጫወት በሚረዳን ልክ ተዘጋጅተናል ብዬ አስባለው።

\"\"

በቅርብ ጊዜያት በብሔራዊ ቡድኑ በተለያዩ ሚናዎች እየተጫወተ ስለመሆኑ…

እግርኳስ ተጫዋች እስከሆንክ ድረስ በሚሰጥህ ቦታ ሁሉ መጫወት ግድ ነው ብዬ አምናለሁ ፤ ለዛም ነው በሚሰጠኝ ቦታ እየተጫወትኩ የምገኘው። ዛሬም አሠልጣኜ በሚሰጠኝ ቦታ ለመጫወት ዝግጁ ነኝ።

ስለተጋጣሚ ቡድን…

የጊኒ ብሔራዊ ቡድን እኔ እያለው ተጫውተን አናውቅም። እኛ ከዚህ ቀደም ከግብፅ እና አይቮሪኮስት ጋር ተጫውተናል ፤ ቡድኑ ከእነሱ እኩል ያለ ቡድን ነው። እኛም በዛ ልክ ነው የምናየው።

የመጨረሻውን የቡድኑን ግብ አንተ ነህ ያስቆጠርከው ፤ ዛሬስ ምን እንጠብቅ ?

ዛሬ ሜዳ ላይ የሚፈጠረው ነገር አይታወቅም ግን ግብ አስቆጥራለው ብዬ አስባለው።

\"\"