\”ብዙ መንገድ ተጉዘን የመጣነው የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ለማድረግ ነው\” ሰዒድ ሀብታሙ

የዋልያዎቹ የግብ ዘብ ሰዒድ ሀብታሙ ከጨዋታው በፊት ተከታዩን አጭር አስተያየት ሰጥቶናል።

\"\"

ለጊኒው ጨዋታ ምን ያህል ተዘጋጅታችኋል ?

ብዙ መንገድ ተጉዘን የመጣነው የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ለማድረግ ነው። እስካሁን ያለው ነገር በጣም አሪፍ ነው። ሁሉም በተነሳሽነት ነው ልምምድ እየሰራ ያለው ፤ ጨዋታውንም በጉጉት እየጠበቅን ያለነው ውጤታማ እንሆናለን ብለን ነው።

ያለደጋፊ ስለመጫወታቸው…

ከደጋፊ ርቀን ነው ጨዋታዎችን እያደረግን ያለነው። ደጋፊ አጠገባችን ቢኖር ኖሮ የበለጠ ደስ ይለን ነበር። አሁን ያ ደጋፊ ከጎናችን እንዳለ እያሰብን ነው እየተዘጋጀን ያለነው።

ባለፉት ጊዜያት ቡድኑ ላይ ስለነበሩ የግብ ዘብ ክፍተቶች…

ሰው በእንቅስቃሴ ላይ ሲሆን መውጣት እና መውረድ ያለ ነው። በህይወት ውስጥ ይህ ያጋጥማል። እኔም በተቻለኝ አቅም ሆነ እንደ ቡድን የተሻለ ውጤት ለማምጣት ጠንክረን እየሰራን ነው። በአጠቃላይ እንደ ቡድን ጥሩ ነገር እናመጣለን ብዬ ነው የማስበው።

\"\"