\”ጨዋታው ቀላል እንደማይሆን ክፍል ውስጥ ተነጋግረን ነው የመጣነው ፤ እኛ ግን ትኩረታችን የራሳችንን አጨዋወት ላይ ነው\” አቤል ያለው

ከምሽቱ የጊኒ ጨዋታ በፊት ከዋልያዎቹ ተጫዋቾች ጋር ቆይታ ማድረጋችን ቀጥሎ አሁን ደግሞ የአጥቂውን አቤል ያለው ሀሳብ ይዘን መጥተናል።

በሀገር ቤት እና ሞሮኮ ለጨዋታው ስላደረጉት ዝግጅት…

ከአዲስ አበባ ጀምሮ ለጊኒው ጨዋታ የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው የምንገኘው። እዚህም መጥተን በሚገባ እየተዘጋጀን ነው። በአጠቃላይ ለጨዋታው በደንብ ተዘጋጅተናል።

\"\"

በብሔራዊ ቡድኑ ከክለብ በተለየ በ9 ቁጥር ሚና እየተጫወተ ስለመሆኑ…

ልክ ነው! በፊት ከመስመር እየተነሳሁ ነው የምጫወተው። ግን ምንም ችግር የለብኝም። አሠልጣኙ የሰጠኝ የጨዋታ መንገድ ስለሆነ ችግር የለውም ፤ ለእኔ ብዙ ልዩነት የለውም።

ወደአፍሪካ ዋንጫ ስለሚያደርጉት ጉዞ…

ከዚህ በፊት አፍሪካ ዋንጫው ላይ ተሳትፈናል። አሁን ግን የተለየ የሚያደርገው በተከታታይ ለመግባት መንገድ ላይ መሆናችን ነው። እስካሁን ዕድሉን አግኝተናል። ከፈጣሪ ጋር ይሄንን ዕድል ለመጠቀም እንደ ቡድን ቆርጠን ነው የተነሳነው።

\"\"

ከተጋጣሚያቸው ሊጠብቃቸው ስለሚችለው ፈተና…

ጨዋታው ቀላል እንደማይሆን ክፍል ውስጥ ተነጋግረን ነው የመጣነው። እኛ ግን ትኩረታችን የራሳችንን አጨዋወት ላይ ነው። ማስቀጠል የምንፈልገው እና ትኩረት የምንሰጠውም በራሳችን አጨዋወት ላይ ነው። የተጋጣሚ ቡድን ጠንካራ መሆን እንዳለ ቢሆንም ትኩረታችንን ራሳችን ላይ አድርገን የቻልነውን ሁሉ አድርገን ጨዋታውን ለማሸነፍ ነው ወደ ሜዳ የምንገባው።