የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመርሐግብር ማሻሻያ ተደርጎበታል

ነገ ቅዳሜ በስድስት ጨዋታዎች በሁለት ሜዳዎች በሚደረጉ ስድስት ጨዋታዎች ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ2014 የውድድር አመት የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ በሀዋሳ ግብርና ሜዳ ላይ ሊደረጉ የነበሩ ሶስት ጨዋታዎች ቀርተው በአርቴፊሻል ሜዳ ላይ የሚደረጉት ሶስቱ የመክፈቻ ጨዋታዎች እንዲደረጉ ማምሻው የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የውድድር ኮሚቴ አሳውቋል

በዚህም መሠረት ነገ ቅዳሜ ታህሳስ 16 የመክፈቻ ሶስት ጨዋታዎች

ሀዋሳ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)

አዳማ ከተማ ከ አቃቂ ቃሊቲ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)

ቦሌ ክፍለከተማ ከ መከላከያ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)

ዕሁድ ታህሳስ 17

አዲስ አበባ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አርባምንጭ ከተማ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)