​ሦስት ወሳኝ ተጫዋቾች ዋልያውን ዛሬ አያገለግሉም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኬፕ ቨርድ አቻው ጋር ዛሬ ምሽት ጭጫታ ሲያደርግ ሦስት ተጫዋቾች በጉዳት ምክንያት ከስብስቡ ውጪ ሆነዋል።

ድረ-ገፃችን በትናንትናው ዕለት ባስነበበችው ዘገባ ሽመልስ በቀለ እና ዳዋ ሁቴሳ የጠንቻ እና የቁርጭምጭሚት ጉዳት በማስተናገዳቸው በዛሬው ጨዋታ ላይሰለፉ ይችላሉ ብላ ነበር። አሁን ከስፍራው ባገኘነው መረጃ መሠረትም ሁለቱም ተጫዋቾች ለጨዋታው ብቁ ባለመሆናቸው ከፍልሚያው ሙሉ ለሙሉ ወጥተዋል።

ከሽመልስ እና ዳዋ በተጨማሪም በመጨረሻዎቹ ልምምድ ላይ መጠነኛ የትከሻ ጉዳት እንዳጋጠመው የሰማነው የግብ ዘቡ ፋሲል ገብረሚካኤልም ህመሙ ለክፉ የሚሰጥ ባይሆንም ለጨዋታ ስለማያደርሰው ከዛሬው ጨዋታ ውጪ እንደሆነ ሰምተናል።