በጌታነህ ከበደ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጉዳይ አዲስ ነገር ተሰምቷል

አጥቂው ጌታነህ ከበደን አስመልክቶ አዲስ መረጃ እየተሰማ ይገኛል።

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ላለበት ሁለት ጨዋታዎች አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ ዝግጅታቸውን መጀመራቸው ይታወቃል።

አስቀድመን እንዳጋራነው መረጃ ከሆነ ሽመልስ በቀለ ፣ ጋቶች ፓኖም ፣ አቡበከር ናስር እና ጌታነህ በቀለ ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ባደረገው ልምምድ አለመገኘታቸውን ዘግበን ነበር። አሁን ደግሞ እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ የአጥቂው ጌታነህ ከበደ ከብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጭ መሆኑ ተሰምቷል።

ጌታነህ ብሔራዊ ቡድኑ ባረፈበት ካኖፒ ሆቴል በዚህ ሰዓት በአካል በመገኘት ከዋልያዎቹ አለቃ ገብረመድህን ኃይሌ ጋር ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ አስቀድሞ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ በማግለሉ ለጨዋታው ዝግጁ አለመሆኑን ተከትሎ ከቡድኑ ጋር አብሮ እንደማይቀጥል አውቀናል።