ኢትዮጵያ በሴካፋ ዋንጫ አትሳተፍም

በኬንያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደውን የሴካፋ ዋንጫ ውድድር ኢትዮጵያ እንደማትሳተፍ ታውቋል።

ከህዳር አስራ አምስት ጀምሮ በኬንያ አስተናጋጅነት የሴካፋ ከ18 ዓመት በታች የወንዶች ውድድር ዘጠኝ ሀገራትን አስትፎ እንደሚጀምር ሴካፋ አሳውቋል። በዚህ ውድድር አስተናጋጇን ኬንያን ጨምሮ ብሩንዲ፣ ሶማሊያ፣ ታንዛንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሩዋንዳ ፣ዛንዚባር፣ ጁቡቲ እንዲሁም በእርስ በእርስ ጦርነት ላይ የምትገኘው ሱዳን ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር እንደማትሳተፍ የተረጋገጠ ሲሆን እንደ ምክንያት የቀረበው የፋይናስ አቅም ማነስ እና የውድድሩ ጠቀሜታ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚያስችል ባለመሆኑ እንደሆነ ሰምተናል።

በቅርቡ የምድብ ድልድል የሚወጣ ሲሆን የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በቀር በዘጠኝ ሀገራት መካከል እንደሚጀመር ይጠበቃል።