ኢትዮጵያውያን ዳኞች የፍፃሜ ጨዋታውን ይመራሉ

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘውን ከ15 ዓመት በታች የሴካፋ ዋንጫ የፍፃሜን ጨዋታ በኢትዮጵያውያን ዳኞች ይመራል።

ከጥቅምት 24 ጀምሮ በሁለት ምድብ ተከፍሎ በስምንት ሀገራት መካከል ሲካሄድ የቆየው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች የዋንጫ ውድድር ነገ ፍፃሜውን ያገኛል። በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የነበረችው ሀገራችን ከምድቡ ሳታልፍ ብትቀርም ሁለቱ ኢትዮጵያን ዳኞች ግን እስከ ፍፃሜው መድረስ ችለዋል።

እስካሁን ባለው ዋና ዳኝነት ሄኖክ አበበ እና ረዳት ዳኝ ወጋየሁ አየለን የግማሽ ፍፃሜ አንድ ጨዋታ ጨምሮ የምድብ ሁለት ጨዋታዎችን በድምሩ ሦስት ጨዋታን መርተው መውጣት የቻሉ ሲሆን አሁን ደግሞ በአራተኛነት እና በረዳት ዳኝነት የፍፃሜ ጨዋታውን እንደሚመሩ ታውቋል። የፍፃሜው ጨዋታ አዘጋጇ ዩጋንዳን ከዛንዚባር ሲያገናኝ ይህንን ጨዋታ ዋና ዳኛ ሄኖክ አበበ በአራተኛ ዳኝነት መመደቡ ሲታወቅ ረዳት ዳኛ ወጋየሁ አየለ ደግሞ በረዳት ዳኝነት እንደተመደበ ታውቋል።