አቡበከር ናስር ወደ ሜዳ ተመልሷል

የብራዚላዊያኑ ኢትዮጵያዊ አጥቂ ከሰባት ወራት በኋላ ተቀይሮ በመግባት ተጫውቷል።

በረዥም ጊዜ ጉዳት ምክንያት ከሜዳ ርቆ የቆየው የሰንዳውሱ አጥቂ አቡበከር ናስር ከወራት ቆይታ በኋላ ወደ ጨዋታ ተመልሷል። ማምሎዲ ሰንዳውን ከሜዳው ውጭ አማዙሉን አሸንፎ መሪነቱን ባጠናከረበት ጨዋታ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ሻሉሊሌን ቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው አቡበከር ከሰባት ወራት በኋላ በሜዳ ላይ ታይቷል። የተጫዋቹ የመጨረሻ ጨዋታ በአፍሪካ ቻምፕዮንስ ሊግ ሰንዳውንስና ዊዳድ ካዛብላንካ ያደረጉት እንደነበር ይታወሳል።

በአዲስ የመለያ ቁጥር የውድድር ዓመቱን የመጀመርያ ጨዋታውን ያደረገው አጥቂው ለቋሚ ተሰላፊነት ከናሚብያዊ ፒተር ሻሉሊ፣ ስያቦንጋ ማቤናና ጊፍት ሞቱፓ ጋር ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።