የአልጄርያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በኢትዮጵያ የመጀመርያ ልምምዱን ሰርቷል

በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚስተናገደው የ2016 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ለማድረግ የአልጄርያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ትላንት ሌሊት 07:00 ላይ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

30 የልኡካን ቡድን በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አልጄርያውያን በሴቶች ብሄራዊ ቡድን የቡድን መሪ ቾል ቤል መሪነት አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ቡድኑ ዛሬ 10:00 ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር ሜዳ ላይ የመጀመርያ ልምምዱን ሰርቷል፡፡ በነገው እለትም በተመሳሳይ ሰአት በአዲስ አበባ ስታድየም ልምምድ ያደርጋሉ፡፡

የአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን የመጀመርያውን ጨዋታ በዴልያ ሮዜኪ የ68ኛ ደቂቃ ጎል 1-0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

በተያያዘ ዜና ቅዳሜ የሚደረገውን የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ መግባታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

PicsArt_1458840840817

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *