የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አልጄርያ ከከተመ 3ኛ ቀኑን ይዟል፡፡ በዛሬው እለትም ጨዋታው በሚደረግበት ሙስታፋ ቻክር ስታድየም ልምምዱን አድርጓል፡፡
በሃገሪቱ ባለው ቅዝቃዜ የተቸገሩት ዋልያዎቹ ከጨዋታው በፊት ባደረጉት የመጨረሻ ልምምዳቸው ቀለል ያሉ ልምምዶችን የሰሩ ሲሆን ቋሚ አሰላለፉን በሚያሳይ መልኩ ለሁለት በመከፈል ተጫውተዋል፡፡ የቆሙ ኳሶች አጠቃቀም ላይም ልምምድ ሰርተዋል፡፡
የብሄራዊ ቡድኑ ረዳት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ወላጅ አባቱ ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው ምክንያት የብሄራዊ ቡድኑን ተለይቶ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል፡፡
የአልጄርያ እና ኢትዮጵያ ጨዋታ በቀዝቃዛማዋ ብሊዳ ከተማ በሚገኘው ሙስጣፋ ሻክር ስታድየም ነገ ምሽት 04:30 ላይ ይካሄዳል፡፡