የአሰልጣኞች አስተያየት | ባህር ዳር ከተማ 1-0 አዳማ ከተማ

ባህር ዳር በሜዳው የመጀመርያ ድሉን ካሳካ በኋላ አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ – ባህር ዳር ከተማ

ስለጨዋታው

“ ባለፈው ካደረግነው ጨዋታ የዛሬው በምንፈልገው መንገድ ሄዷል ማለት አልችልም። ግን ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ከነበረን ፍላጎት የተበሳ ልጆቼ ላይ የመዘበራረቅ ነገር ነበር። ይህም ገመጓጓት የተነሳ ነው። በተረፈ በጊዜ ያገባነውን አስጠብቆ ለመውጣት እና ሦስት ነጥብ ይዞ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ልጆቹ ያድጉትን ጥረት አደንቃለው። ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ አሸናፊነት በመመለሳችን እስካሁን በትዕግስት ይጠብቁን የነበሩ ደጋፊዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለው።

ስለተጫዋች አጠቃቀም

“ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ከፍፁም ውጪ የገባው ምርጡ አስራ አንድ እየመጣን ነው። እንግዲህ እግርኳስ ሂደት ነው። አሁን ግን ባለፈው ሦስት ጨዋታ የተጫወተው የቡድናችን ምርጥ ነው።

ስለማጥቃት መንገድ

“ በቀጣይ ውጤቱ ያስፈልገናል ፤ ደረጃችንን ከፍ ለማድረግ። በቀጣይም ከመቋረጡ በፊት ከሲዳማ ጋር በሚኖረን ጨዋታ ከዚህ ቀደም ያደረግናቸውን ጨዋታዎች ስህተትን አረመን ነው የምንገባው። አሁንም በማጥቃት ላይ መሰረት ያደረገ ጨዋታ ተጫውተን ሦስት ነጥብ ለማግኘት እንዘጋጃለን።

ስለደጋፊዎቹ

“ከጀርባችን ሆኖ ለዛሬው ውጤት መገኘት ብቻ አይደለም ሜዳችን ላይ ላሳየናቸው እንቅስቃሴዎች ትልቁ ኃይል ነበር። ሁሉንም አመሰግናለው።”

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – አዳማ ከተማ

ስለጨዋታው

“ ሁለተኛው አጋማሽ ትንሽ ውጥረት የበዛበት ነበር። በመጀመርያው ግን የተሻለ ሆነን የጎል ዕድሎች ባገኘንበት ሰዓት ማስቆጠር አልቻልንም። የጨዋታው ውጤት የተወሰነው እኛ በምንፈልገው መንገድ ጨዋታውን ጀመርን ዕድሎችን መጠቀም አልቻልንም። ተጋጣሚያችን ያንን ጎል አገባ። ዘጠና ደቂቃ ጨዋታው በመቆራረጥ አልቋል። በተለይ ሁለተኛው አጋማሽ ብዙ ተጫዋቾች ሜዳው ላይ ይወድቁ ነበር።

ስለሳኩቡ ካማራ

“ እንግዲህ ፊልሙን አላየሁትም። ባዛ ርቀት ለምን ጎሉን ለቆ እንደወጣ መናገር አልችልም።

ስለመሰናበት ስጋት

“ምንም ጥያቄ የለውም። ሳይታሰብ ወደ ወራጆቹ ተጠግተናል። የተጫዋቾችን ሥነ ልቦና ከፍ በማድረግ ከወራጅ ክልል ለመውጣት በስህተቶቻችን ላይ ጠንክሮ መስራት ነው።

ስለአጥቂዎች አጋጣሚ አለመጠቀም

“በየጊዜው የጎል ዕድሎችን እንዴት እንደምንፈጥር እና ጎል የማግባት ሥነ ልቦናቸውን ከፍ ለማድረግ ደጋግመን እየሰራን ነው። ዛሬም ግልፅ ዕድሎችን አግኝተን ስተናል እንደ ሁልጊዜው። እንግዲህ ጠንክሮ መስራት ነው።”