የአቡበከር ናስር የደቡብ አፍሪካ ጉዞ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ጨዋታውን ዛሬ ያከናወነው አቡበከር ናስር ወደ ደቡብ አፍሪካ ይጓዛል።

ከደቡብ አፍሪካንው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ጥር ወር ላይ የቅድመ ስምምነት አጠናቆ የመጣው አቡበከር ናስር የዝውውር ሂደቱን ለማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ ማምሻውን እንደሚመለስ ከሰዓታት በፊት መረጃ ማድረሳችን ይታወቃል።

ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ
ከዕረፍት መልስ በፍፁም ቅጣት ምት ቡድኑን አቻ ያደረገው አቡበከር ነገ ወደ ደቡቡ አፍሪካ እንደሚጓዝ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል። በደቡብ አፍሪካ የስምንት ቀን ቆይታ እንደሚኖረው የገለፀው አቡበከር ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ያለውን የዝውውር ሂደት ሙሉ ለሙሉ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች የአቡበከርን አገልግሎት የማያገኝ እንደሆነ ተረጋግጧል። በዚህም አቡበከር አንዳንድ ሁኔታዎች አስገድደውት በዛው የሚቆይ ከሆነ እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻው ድረስ እንደማይኖር ተገምቷል።