ኢትዮጵያ ቡና ከአማካይ ተጫዋቹ ጋር ለመለያየት ተስማምቷል

የዝውውር መስኮቱ ሊከፈት ሰዓታት በሚቀሩበት ወቅት ኢትዮጵያ ቡና ከአንድ ተጫዋቹ ጋር ለመለያየት ተስማምቷል።

ኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ ዓመት ራሱን አጠናክሮ ለመቅረብ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ መጀመሩ እና ከነገ ጀምሮ በሚከፈተው የዝውውር መስኮት ከዋና አሰልጣኝ ቅጥር ጀምሮ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ በቡድኑ ውስጥ ቀሪ የውል ዘመን ካላቸው ተጫዋቾች ጋር መለያየትም ይጀምራል።

ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ ያለፉትን ሦስት ዓመታት በቡድኑ ውስጥ በአማካይ ተጫዋችነት ያገለገለው ታፈሰ ሰለሞን ምንም እንኳን በክለቡ የሚያቆየው ቀሪ ሁለት ዓመት ኮንትራት ቢኖረውም በስምምነት ለመለያየት መነጋገሩን እና ነገ ወደ ፌዴሬሽን በማቅናት ሁለቱ አካላት ውላቸውን አራት ሺህ ብር በመክፈል እንደሚቀዱ ተጫዋቹ ነግሮናል።

ኢትዮጵያ ቡናን በተመለከተ ከነገ ጀምሮ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎች ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።