ጦሩ ከአጥቂው ጋር ተለያይቷል

ከወራት በፊት መከላከያን የተቀላቀለው ጊኒያዊው አጥቂ ውሉን በስምምነት ቀዶ ዛሬ ወደ ሀገሩ አምርቷል።

የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ነገ ከመከፈቱ በፊት በርካታ ክለቦች የነባር ተጫዋቾችን ውል ለማደስ፣ የማይፈልጓቸውን ለመሸኘት እና አዲስ የሚያመጧቸውን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። ሊጉን ዘንድሮ ተቀላቅሎ በመጨረሻዎቹ ሳምንታት መክረሙን ያረጋገጠው መከላከያ በውድድር አጋማሹ የዝውውር መስኮት ካስፈረመው ተጫዋች ባዳራ ናቢ ሲላ ጋር ገና አራት ወር ሳይሞላው በስምምነት መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በሊጉ 415 ደቂቃዎችን የተጫወተው ቁመታሙ አጥቂ አንድም ጎል ያላስቆጠረ ሲሆን ለግብ የሚሆን ኳስም አመቻችቶ አላቀበለም። ከሰሞኑን ከክለቡ ጋር ሲነጋገር ቆይቶ ዛሬ ውሉን ቀዶ ወደ ሀገሩ እንዳመራ ታውቋል።