ወጣቱ ተከላካይ የፈረሰኞቹ የመጀመርያ ፈራሚ ለመሆን ከጫፍ ደርሷል

ለቀጣይ ዓመት ራሳቸውን ለማጠናከር ወደ እንቅስቃሴ የገቡት ፈረሰኞቹ የመጀመርያ ፈራሚያቸው ለማግኘት ተቃርበዋል።

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በመሾም እና በቀጣይ ዓመት ወደ ቡድኑ በሚመጡ ተጫዋቾች ዙርያ ባሳለፍነው ቅዳሜ የክለቡ የቡርድ አመራሮች ስብሰባ መቀመጣቸውን እና ከዛሬ ጀምሮ ወደ ዝውውሩ እንደሚገቡ በትናትናው ዕለት መዘገባችን ይታወቃል።

በዚህም መነሻነት የፈረሰኞቹ የመጀመርያ ፈራሚ ወጣቱ የመስመር ተከላካይ ረመዳን የሱፍ ለመሆን መቃረቡን ለማወቅ ችለናል። ክለቡ እና የመስመር ተከላካዩ በአብዛኞቹ ጉዳዮች የተስማሙ ሲሆን የዝውውሩ ሁኔታውንም በቅርቡ ክለቡ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

በንግድ ባንክ የተገኘው ረመዳን በስሑል ሽሬ፣ በወልቂጤ ከተማ የተጫወተ ሲሆን ተፈጥሯዊ የግራ እግር ተጫዋች ሲፈልግ ለነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጥሩ አማራጭ እንደሚሰጥ ይታሰባል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀሩት ቀናት ወደ ቡድናቸው የሚቀላቀሉ ሦስት ከፍተኛ ዝውውር ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።