ሙጂብ ቃሲም ወደ ሀዋሳ ከተማ?

ሁለገቡ ተጫዋች ሀዋሳ ከተማን ለመቀላቀል በቃል ደረጃ መስማማቱን ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቁሟል፡፡

በ2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር ገበያው የገባው ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች ለማስፈረም በቃል ደረጃ ስምምነት መፈፀሙን አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ እና የክለቡ ቦርድ አባል ባዩ ባልጉዳ ለሶከር ኢትዮጵያ በላኩት መረጃ ገልፀዋል፡፡

በፋሲል ከነማ ስኬታማ ቆይታን ያደረገው ሙጂብ በአልጄሪያው ክለብ ጄ ኤስ ካቢሌ አጭር ቆይታን አድርጎ ዳግም በመመለስ በፋሲል ከነማ ሁለተኛውን ዙር ግልጋሎት የሰጠ ሲሆን በሲዳማ ቡና አብሮት መጫወት ከቻለው ዘርአይ ሙሉ ጋር በጋራ ለመስራት ወደ ቀድሞው ክለቡ ለመመለስ የቃል ስምምነት ላይ መድረሱ ታውቋል። ምናልባት ነገ ጠዋት በሚደረግ ውይይት የዝውውሩ የመጠናቀቅ እና አለመጠናቀቅ ጉዳይ የሚለይ ይሆናል።