ከነዓን ማርክነህ ወደ መከላከያ አምርቷል

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ቻምፒዮን የሆነው ከነዓን ማርክነህ የመከላከያ ተጫዋች መሆኑ እርግጥ ሆኗል።

በዝውውር ገበያው በዛሬው ዕለት መሳተፍ የጀመሩት መከላከያዎች በይፋ የበረከት ደስታን ዝውውር ማገባደዳቸውን ከሰዓታት በፊት ዘግበን ነበር። ከበረከት ጋር ለመከላከያ ፊርማውን ለማኖር ወደ ፌዴሬሽን አምርቶ የነበረው ከነዓን ማርክነህም ቅድመ ስምምነቱን ቢፈፅምም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለው ውል የሚጠናቀቀው ነሐሴ 30 መሆኑን ተከትሎ ከቅድሞ ክለቡ መልቀቂያ እንዲያመጣ እንደተደረገ አውቀናል።

ከአዳማ ወጣት ቡድን ተገኝቶ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ከተማ ከዛም ዳግም አዳማ ከተማን በመቀላቀል የእግር ኳስ ህይወቱን ቀጥሎ የነበረው ከነዓን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለው ውል ተጠናቆ ከክለቡ ጋር ከሰሞኑን ድርድር ሲያደርግ ቢቆይም ውይይቱ አለመሳካቱን ይታወቃል። በቀጣይ ቀናት መልቀቂያውን ሲያመጣም የጦሩ ህጋዊ ተጫዋች እንደሚሆን ታውቋል።