መከላከያ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ከሰዓታት በፊት ወደ ዝውውሩ የገቡት ጦረኞቹ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አክለዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር ገበያው ጎራ በማለት በረከት ደስታን የመጀመሪያ ፈራሚ ያደረጉት መከላከያዎች ሁለት ተጨማሪ አዳዲስ ፈራሚዎችን በሁለት ዓመት ውል አስፈርመዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከተገኘ በኋላ ለሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድኖች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወጣት ቡድን  እናም በቅርቡ በዋልያዎቹ ስብስብ ተካቶ የነበረው ወጣቱ ግብ ጠባቂ ዳግም ተፈራ ከዲላ ከተማ የከፍተኛ ሊግ ቆይታ መልስ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሀዋሳ ተመልሶ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት የቆየው ሲሆን በዛሬው ዕለት መከላከያን ተቀላቅሏል፡፡

ሳሙኤል ሳሊሶ ወደ ቀድሞው ክለቡ የተመለሰ ሌላኛው ተጫዋች ነው፡፡ በመከላከያ ለሁለት ጊዜያት ያህል መጫወት የቻለው እና የዘንድሮው የውድድር ዘመን ወደ ታችኛው የሊግ ዕርከን በወረደው ሰበታ ከተማ ያሳለፈው የመስመር አጥቂው መዳረሻው ጦሩ ሆኗል፡፡