የዋልያዎቹ ተጋጣሚ የመጨረሻ ስብስቧን ይፋ አድርጋለች

ሐምሌ 15 እና 21 በቻን ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥሙት ደቡብ ሱዳኖች የመጨረሻ ስብስባቸውን ይፋ አድርገዋል።

በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የቻን ውድድር ላይ የሚሳተፉ ብሔራዊ ቡድኖችን ለመለየት የማጣሪያ ጨዋታዎች ከቀናት በኋላ መደረግ ይጀምራሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ለሁለቱ ጨዋታዎች ይህንን ዘገባ በምንሰራበት ሰዓት የመስክ ላይ ልምምዱን ማድረግ ጀምሯል። ተጋጣሚው ደቡብ ሱዳን በበኩሏ ለበርካታ ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ልምምዷን ከጀመረች ቀናቶች የተቆጠሩ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊትም ለፍልሚያዎቹ የምትጠቀምበትን የተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ አድርጋለች።

በስቴፋኖ ኩዚ የሚመራው ቡድኑ ታንዛኒያ ላይ ለሚደረጉት ጨዋታዎች ከነገ በስትያ ወደ ስፍራው የሚያቀና ይሆናል። ምናልባትም ዳሬ ሰላም ላይ ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን እንደሚያደርግም ይጠበቃል።

ከስር የተመረጡት ተጫዋቾች ተቀምጠዋል