ዐፄዎቹ የመሀል ተከላካይ አስፈርመዋል

የነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ ተጠምደው የነበሩት ፋሲል ከነማዎች በዝውውሮ መስኮቱ የመጀመሪያ ተጫዋቻቸውን አስፈርመዋል።

የቡድናቸውን ሁነኛ የመሀል ተከላካይ እና አምበላቸው የነበረውን ያሬድ ባየህን ለባህር ዳር ከተማ አሳልፈው የሰጡት ፋሲል ከነማዎች በምትኩ መናፍ ዐወልን ከባህር ዳር ከተማ ማስፈረማቸውን ታውቋል።

ከአዳማ ከተማ የእድሜ እርከን ቡድን ከተገኘ ወዲህ ፈጣን እድገትን በማሳየት በአዳማ ከተማ ዋና ቡድን እና ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ደግሞ በባህር ዳር ከተማ ጥሩ የሚባልን ጊዜ ያሳለፈው መናፍ ዐወል በተወሰነ መልኩ የተጫዋቾች መለዋወጥ በዝቶበት ለነበረው የፋሲል የመሀል ተከላካይ ክፍል መረጋጋትን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

ቡድኑም በቀጣይ በለቀቁበት ተጫዋቾች ምትክ ተጨማሪ ተጫዋቾችን ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።