ኢትዮጵያ መድን ተጨማሪ ሦስት ተጫዋቾች አስፈርሟል

ከደቂቃዎች በፊት ቴዎድሮስ በቀለን ያስፈረሙት ኢትዮጵያ መድኖች ተጨማሪ ሦስት ተጫዋቾችን የግላቸው አድርገዋል።

የመጀመሪያው የቡድኑ ፈራሚ አማካዩ ዮናስ ገረመው ነው። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቡና ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ሲዳማ ቡና ያሳለፈው አማካዩ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በአዳማ ቆይታ ማድረጉ አይዘነጋም።

አማካይ ክፍል ላይ ሌላው ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋቾች ሀብታሙ ሸዋለም ሆኗል። የቀድሞው የወልዲያ ከተማ እና ስሁል ሽረ ተጫዋች በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ደግሞ በወልቂጤ ከተማ የአማካይ ክፍል ላይ በወጥነት ቡድኑን ማገልገል ችሏል።

ሌላኛው የቡድኑ ፈራሚ ደግሞ የፊት መስመር ተሰላፊው ሀቢብ ከማል ነው። ከኢትዮ ኤሌክትሪክ የእድሜ እርከን ቡድን የተገኘው ተጫዋቹ በከፍተኛ ሊግ በኮልፌ ቀራንዮ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ደግሞ በፕሪምየር ሊጉ በአርባምንጭ ከተማ የተሳካ ጊዜያትን ማሳለፉ አይረሳም።