ሲዳማ ቡና አማካይ ተጫዋች አስፈርሟል

በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በስምምነት የተለያየው ተጫዋች ማረፊያው ሲዳማ ቡና ሆኗል።

በአሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ የሚመራው ሲዳማ ቡና ወደ ዝውውሩ በመግባት የተለያዩ ተጫዋቾችን እያስፈረመ ይገኛል። አሁን ደግሞ የአማካኝ ስፍራ ተጫዋቹን አቤል እንዳለን ማስፈረሙ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የእግርኳስ መነሻውን በማድረግ በደደቢት ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ዘንድሮ ለኢትዮጵያ ቡና ሲጫወት የቆየው አቤል ከቡናማዎቹ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ ለሁለት ዓመት ለመጫወት ለሲዳማ ቡና በዛሬው ዕለት ፊርማውን አኑሯል።