ተመስገን ዳና በይፋ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ሆኗል

ኢትዮጵያ ቡና አሰልጠኝ ተመስገን ዳና አዲሱ አሰልጣኙ አድርጎ መሾሙን አሳውቋል።

በተለያዩ መንገዶች የአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ምትክ ይሆናል ተብሎ ሲነገርለት የነበረው አሰልጣኝ ተመስገን ዳና በይፋ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ መሆኑ ተረጋግጧል። አሰልጣኝ ተመስገን በኢትዮጵያ ቡና ለሁለት አመት የሚያቆየውን ውልየፈፀመ ሲሆን በቀጣይ ቀናት አብረውት የሚሰሩትን ምክትሎቹን ያሳውቋል ተብሎ ይጠበቃል።

አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ከተማ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖችን በማሰልጠን ጥሩ ስም ያተረፈ ከመሆኑ ባሻገር በከፍተኛ ሊግ በደቡብ ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ከ17 እና 20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ሲያሰለጠን የቆየ ሲሆን በዘንድሮ የውድድር ዓመት በወልቂጤ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ መስራቱ ይታወሳል።